SunFlare Co., Ltd.

Global Interface & Solutions

ለበርካታ ዓመታት የትርጉም ኤጀንሲ ሆኖ በመስራት ጠንካራ ልምድ ያካበተው SunFlare፣ ለደንበኞቹ አስተማማኝ አዕምሯዊ አጋር እንደሆነ ለመቀጠል ቁርጠኛ ነው።
በሁሉም የስራ መስኮች ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ኩባንያዎችን የሰነድ ፍላጎቶች ለማሟላት ተስማሚ እንዲሆኑ ተደርገው የተዘጋጁ ሁለገብ አገልግሎቶችን እናቀርባለን።
ከስነዳ ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶችን በፍጥነት እና በትክክል በመለየትና በማስተካከል ለደንበኞቻችን ምርጥ የሆኑ መፍትሄዎችን ማቅረብ እንችላለን።

በ ISO 27001 እና በ ISO 9001 የተመሰከረለት

ደንበኞቻችን የተለያዩ የስነዳ ፍላጎቶች አሏቸው። ይህንን ለማረጋገጥም ሚስጥራዊ የደንበኛ መረጃን ለመቀበል እና ለመስጠት የሚያስችል ከፍተኛ የደህንነት ማዕቀፍ ያለን ሲሆን፣ በዚህም ከፍተኛውን የጥራት ደረጃ ለማቅረብ ስንችል፣ የተለያዩ የአለም አቀፍ ስራ አመራር ስርዓቶችንም እንከተላለን።

በበርካታ ኢንዱስትሪዎች፣ ንግዶች እና ዘርፎች ልምድ ያካበተ

አስተማማኝ የንግድ አጋር እንደሆንን መቆየታችንን ለማረጋገጥ፣ የኢንዱስትሪ ባለሙያዎቻችን እና የመስክ ስፔሻሊስት ቡድኖቻችን ደንበኞቻችን ለሚገጥሟቸው ተግዳሮቶች ምርጥ መፍትሄዎችን ለማቅረብ በጋራ ይሰራሉ።

ከ 90 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ብቃት ያለው

አንድ ኩባንያ በራሱ በዓለም አቀፍ አውድ ውስጥ ንግዱን መገንባት ከፈለገ፣ የሁሉንም ታላሚ አገሮች ቋንቋዎችና ባህሎች ማወቅ ይኖርበታል። ይህ ለንግድ ስራ በጣም ተግባራዊ አቀራረብ እንደማይሆን ግልጽ ነው።
በ SunFlare ግን፣ ከ 90 በሚበልጡ ቋንቋዎችና ቋንቋዎቹ ጥቅም ላይ የዋሉባቸውን ቦታዎች ባህል ጭምር የሚያውቁ ባለሙያዎች አሉን። ደንበኞቻችን እንደ ዓለምአቀፍ ንግድነት ስኬታማ ለመሆን የሚያስችላቸውን ታላሚ እና ወቅታዊ ድጋፍ መስጠት ይችላሉ። ባለሙያዎቻችን በላቀ የቋንቋ ክህሎቶች የተደገፈ መጠነ ሰፊ መስክ-ተኮር ዕውቀት ያላቸው ሲሆን፣ ይህም እንደ የህግ ሰነዶች፣ የጆርናል ጽሁፎች እና የቁጥጥር ማመልከቻዎችን የመሳሰሉ ከፍተኛ የሙያ ደረጃን ለሚጠይቁ ሰነዶች ከፍተኛ ጥራት ያላቸው አገልግሎቶችን እንድናቀርብ ያስችለናል።

የኮርፖሬት ፕሮፋይል

የኮርፖሬት ስም

SunFlare Co., Ltd.

የተመሰረተው

ኦገስት 1, 1971

አድራሻ

የቶኪዮ ዋና መስሪያ ቤት
Shinjuku Hirose Bldg., 4-7 Yotsuya, Shinjuku-ku,
Tokyo 160-0004, Japan

ዋና ዳይሬክተር

Hiroyuki Sasai

ቢዝነስ

ስነዳ

 • ትርጉም
 • ሎካላይዜሽን
 • ጽሑፍ (ቴክኒካዊ እና ህክምና)
 • የፈጠራ አገልግሎቶች (ንድፍ፣ DTP፣ ድር እና ቪዲዮ)

ማማከር

 • የስነዳ ማማከር
 • ምርምር (ህጎች፣ ደንቦች፣ መስፈርቶች እና የባለቤትነት መብቶች)
 • የፋይል እና የማመልከቻ ድጋፍ (ፓተንት፣ የቁጥጥር ጉዳዮች እና የህክምና መሳሪያዎች)

ትምህርት እና ስልጠና

 • SunFlare Academy
 • የተርጓሚ ብቃት ፈተና (TQE)
 • የኮርፖሬት ስልጠና
 • ሴሚናሮች (ፓተንቶች እና የህክምና መሳሪያዎች)

የዕውቅና ማረጋገጫ

ISO 27001, ISO 9001, ISO 17100 and Privacy Mark (JIPDEC)
ለሕክምና መሣሪያዎች ፈቃድ የአይነት II የገበያ ፈቃድ ባለቤት

Back to Top